ሼይኻ ፋጢማ የአይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት አዲስ አበባ

ሼይኻ ፋጢማ የአይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት አዲስ አበባ post thumbnail image

የአይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት

በሼይኻ ፋጢማ የአይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት የተፈጠረውን ሁኔታ ፌደራል መጅሊሱ አጣርቶ ካቀረበ የተከሰተው ችግር እንደሚፈታ የአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት አዳነች አበቤ ገለፁ

  • ሀሩን ሚድያ ሕዳር 17/2017

ሀሩን ሚድያ በሸይኻ ፋጢማ የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ሙስሊም ተማሪዎች በደል እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተደጋጋሚ ዘገባዎችን መስራታችን ይታወሳል።

በሸኻ ፋጡማ የአይነስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች የ5 ወቅት ሶላት በግቢ ውስጥ እንዳይሰግዱ በመከልከላቸው የሀይማኖት ጥቃት እየተፈፀመባቸው ስለሆነ መፍትሄ እንዲሰጥ የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ለከንቲባዋ ጥያቄ አቅርበዋል።

የተፈጠረውን ቦታው ድረስ በመሄድ አጣርታችሁ ካቀረባችሁ የተከሰተው ችግር እንዲፈታ እንደሚደረግ ከንቲባዋ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር ዶ/ር ሽህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራ ከፍተኛ የም/ቤቱ አመራሮች ከክብርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄዎች የቀረቡ፥ ያልተፈቱ እና አዲስ ጥያቄዎችን አስመልክቶ ህዳር 16/2017 ስድስት ዋና ዋና ጥያቄዎችን አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡

በነበረው ስብስባ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ካነሳቸው ጥያቄዎች መካከል፦

  1. የከተማ አስተዳደሩ የሙስሊሙን ማህበረሰብ በተለያዩ የከተማው የሹመት ቦታዎች አካታችና አሳታፊነት ምን ይመስላል? በቀጣይስ ምን ታስቧል?
  2. ከዚህ በፊት በደብዳቤ የጠቅላይ ም/ቤቱ አሁን ካለበት ቦታ በከተማው መሐል ዋና ቢሮ መስሪያ የሚሆን ቦታ ጥያቄ አቅርበን ምላሽ አልተሰጠበትም፣ እንዲሁም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 13 ቁጥር ማዞሪያ ወደ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን እስከ ካርል አደባባይ ዞሮ እስከ ኦሜጋ ትምህርት ቤት ድረስ አካባቢ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለረጅም ጊዜ ሲጠይቅ የነበረው የ5 ወቅት ሶላት የሚሰግድበት ቦታ ባለመኖሩ ጥያቄውን አቅርበን እስካሁን ምላሽ አልተገኘም።
  3. ጠቅላይ ም/ቤቱ ቋሚ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር በከተማው መሐል ቦታ በማግኘት ትልቅ ህንፃ በመገንባት የገቢ ምንጩን በአገር ውስጥም ለማድረግ የቦታ ጥያቄ አቅርበናል።
  4. በዱባይ ንጉስ እናት በሸይኻ ፋጡማ አማካኝነት በአገራችን ለሚገኙ አይነ ስው ደረጃው የጠበቀ የአይነስውራን ት/ት ቤት ተገንቦቶ ሁሉንም ማህበረሰብና የእምነት ተከታይ እንዲጠቀሙብት መደረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም በትምህርት ቤቱ የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች የሃይማኖት ስርዓት ግዴታ የሆነውን የ5 ወቅት ሶላት በግቢ ውስጥ እንዳይሰግዱ በመከልከላቸው የሃይማኖት ጥቃት እየተፈፀማባቸው ስለሆነ ይህን ጉዳይ እልባት እንዲሰጥበት።
  5. የታላቁ ነጃሺ መስጅድና ኢስላማዊ ማዕከል የተሰጠው ቦታ 30,000 ካ.ሜ ቦታ በካርታ ቢሆንም በአጐራባች የተያዙ ቦታዎችን ባለመረከባችን ምክንያት ግንባታውን ለማካሄድ ተቸግረናል።
  6. የጠቅላይ ም/ቤቱን ምርጫ አስመልክቶ በሚቀጥለው ጊዜ የሦስት አመት ጊዜያቸውን የሚያጠናቅቁ አመራሮች ለመተካት ምርጫ ለማካሄድ በጠቅላይ ም/ቤቱ እቅድ የተያዘ ስለሆነ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍና እገዛ እንዲያደርግልን።

በእነዚህ በቀረቡት አምስት ጉዳዮች ላይ ከክብርት ከንቲባ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ሁሉንም ደረጃ በደረጃ በአስተዳደሩ በኩል በአጭር ጊዜ ምላሽ እንደሚሰጥና በሸይኻ ፋጡማ የተፈጠረውን ቦታው ድረስ በመሄድ የተፈጠረውን ሁኔታ አጣርታችሁ እንድናቀርብና የተከሰተው ችግር እንዲፈታ እንደሚደረግ ገልፀዋል። በቀጣይም በመገናኘት የተጠየቁና የሚጠየቁ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሄ እንደሚሰጥባቸው ገልፀዋል።

በጠ/ም/ቤቱ በኩል ጉዳዩን በመከታተል የተደረሰበትን ለህዝበ ሙስሊሙ እናሳውቃለን ማለታቸውን የዘገበው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ነው።

© ሀሩን ሚድያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

Be carfullBe carfull

Be carefull be carefull! Do not cry weak~Don’t trust in your power, your power, your side, your wealth, and push people. “My lord! I am powerless, judge me!” Woe to

AqeedahAqeedah

Aqida How much did the Sohaba care about the Muslim faith?~Those lions of Islam, the wonderful companions of the Prophet ﷺ, sacrificed everything they could to protect the Aqeedah of